በአራት የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ እድገትና ብልጽግናን የሚያመጣ የፌዴራል ስርዓት መገንባት ዋነኛ አላማው መሆኑን አስታወቀ። በሃገራዊ ንቅናቄው የምስረታው ስነስርዓት ላይ ያወጣው የጋራ መግለጫ እንደሚያመለክተው ብሄር ብሄረሰቦች መብታቸው የተከበረባትና ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን መመስረት የህብረቱ ዋነኛ ዓላም መሆኑ ታውቋል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ በአርበኞች ግንቦት ሰባት፣ በአፋር ህዝብ ፓርቲ፣ እና በሲዳማ ህዝቦች ዴሞክራሲያው […]
