የአለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) ኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆዎርናሊስትስ የኢትዮጵያ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሁሉም ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሃሙስ ጥሪውን አቀረበ። በሃገሪቱ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ወከባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ድርጅቱት ለመንግስት ባቀረበው የጸሁፍ መልዕክት አመልክቷል። ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ አንድ ጋዜጠኛን ጨምሮ ሁለት ጦማሪያን ለእስር መዳረጋቸውን ያወሳው ሲፒጄ ሌላ […]
