ብአዴን 36ኛ ዓመቱን ለማክበር በዓለማያ ዩንቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎችንና በሐረር ከተማ ይደግፉኛል ያላቸውን ነዋሪዎች ሰብስቦ ለማነጋገር ኅዳር 9 እና 10 ቀን 2009 ዓም ሙከራ አድርጎ ነበር። ከዓለማያ ዩንቨርሲቲ ዋና እና ሐረር ግቢዎች ተማሪዎችን ወደ ቤተ መንግሥት አዳራሽ የሚወስዱ ዐሥር አውቶቢሶችን ዩንቨርሲቲው መድቦ ነበር። የዐማራ ተማሪዎች “እናንተ እነማን ናችሁ የምትሰበስቡን? ለዐማራ ሕዝብ ሳትቆሙ የ36 ዓመት ጎልማሳ ነን […]
