ለሦስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መነሳት ከነሐሴ 15 እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተደረገው ግምገማ ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ለእያንዳንዳቸው መነሳት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ አንድ ዓመት ያልሞላቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ሲሆኑ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና በተመሳሳይ ማዕረግ የግብርና ቢሮ […]
