በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በጽኑ እስራትና በገንዘብ የተቀጡት የአውራ አምባ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ፣ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ አንድነት ፓርቲ (መኢዴአፖ) ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሔርና ሒሩት ክፍሌ፣ መንግሥት ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ከዓመት በፊት ለፌዴራል ይቅርታ ቦርድ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡ ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የአገሪቱን ሕገ መንግሥትና ሕግ ለማፈራረስ፣ በዜጎችና በመንግሥት ተቋማት ላይ ጉዳት ለማድረስ […]
