አዲስ ዓመት ለኔ ባለውለታዬ ነው፡፡ ለምን ብትሉ ውኃ ኣጣጬን ያገኘሁት የዛሬ ዓመት ልክ በዚህ ጊዜ ነበርና፡፡ ትዝ ይለኛል የዛሬ ዓመት ይኼን ጊዜ አከራዬ እትዬ በላይነሽ ንግግራቸውን እያጣፈጡ፣ “ሸጋው ወንደላጤ እንግዲህ አዲስ ዓመት በደጅህ ነው” አሉ፡፡ ደነገጥሁ፡፡ የቤት ኪራይ መጨመሪያ ስልታቸው መቼም አያልቅም፡፡ አሁን ለታ የወረዳችን ዋና አውራ ጎዳና በኮብልስቶን በመሠራቱ ምክንያት፣ “ከዚህ በኋላ ጭቃ ስለማያስቸግራችሁ ኪራይ […]
