ከ130 ሰዎች በላይ ሕይወትን የቀጠፈው የቆሼ አደጋ ሁለት ወራት ቢያልፉትም፣ እስካሁን ድረስ ቃል የተገባው ዕርዳታ እንዳልደረሳቸው በአደጋው ተጎጂ የሆኑ ግለሰቦች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ አደጋው በተከሰተ ማግሥት ማለትም መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. በነበሩ ሁለትና ሦስት ሳምንታት፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ዕርዳታ እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡ ከመንግሥትና ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ተቋማት፣ እንዲሁም ከባለሀብቶች ወደ 75 […]
