ዩናይትድ ስቴትስ ከፓሪሱ ዓለምቀፍ የአየር ንብረት ስምምነት እንድትወጣ መወሰናቸውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ፡፡ ፕሬዚዳንት ይሔን ያስታወቁት ከዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት በጠሩት ሥነ ስርዓት ላይ ሲሆን ከስምምነቱ የሚወጡት የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት እጄ ሰባራ ያደራጋል ብለው በማመናቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ይሕ 195 ሀገሮች የፈረሙት ስምምነት በመጭዎቹ ሃያ ሁለት ዓመታት በዩናይትድ ስቴትስ ምጣኔ ሀብት ላይ የ3 ቲሪሊዮን ዶላር ጉዳት […]
