የግብጽ ባለስልጣናት በመገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ ውሃ መሙላት በሚጀምርበት የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ገለጹ። የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከዚህ በፊት በሁለቱ ሃገራት መካከል ሲካሄድ በቆየ ድርድርና ስምምነት ወቅት ግድቡን በውሃ የመሙላቱ ሂደት እንዲዘገይ ጥያቄን ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። የግብፅ ባለስልጣናት ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ በጥናት ተደግፎ እስኪቀርብ ድረስ የግድቡ የግንባታ […]
