የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ሀገራቸው ላይ ተፈጽሟል ላሉት በደል በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ያላቸውን ተፅዕኖ በመጠቀም ካሣ እንዲያስከፍሉ ለብዙ መንግሥታት መሪዎች ዛሬ መልዕክት ልከዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት፣ የሀገሮችን ሠላምና ፀጥታ በማስከበር ለዓለም ድኅንነት የመሥራት ቀዳሚ ኃላፊነትና ሕጋዊ ግዴታም እንዳለበት በመልክታቸው አስምረውበታል፡፡ የፕሬዚዳንቱ ስሞታ እአአ ከግንቦት 1998 እስከ 2000 በሀገራቸውና […]
