ትላንት ማክሰኞ (ህዳር 24, 2006 ዓም) በኢትዮጵያ ስዓት አቖጣጠር ልክ ከ10:00ጀምሮ ለተለያዩ የማህበራት አመራሮችና እድሮች ዛሬ ሮብ ለሚደረግ ስብሰባ ሰዉ እንዲጠሩ መልዕኽት ተላለፈ። መልዕክቱ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለች የሚመሩትና ሌሎች ሚንስትሮች የሚገኙበት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ5:00 የሚጀመር ስብሰባስላል ከየማህብራችሁ 200 ሰዉ እንድትጋብዙ የሚል በስልክ መደወል ተጀመረ። በተሰጠዉ መምሪያ መሰረት ሁሉም አመራሮች ወደ አባሎቻቸዉ መደወል ያዙ። […]
