ህዳር 29 በደረሰ ቁጥር ኢህአዴግ ሳያውቀው የሚዘምረው አንድ መዝሙር አለው፡፡ ‹‹አገር ማለት ሰው ነው….ሰው ነው ሰው ነው አገር…››፡፡ በእርግጥ እንዲሁ ላዳመጠው መዝሙሩ ይስባል፡፡ ይህ መዝሙር ኢህአዴግ ለአገሪቱ ዳር ድንበር እንደማይጨነቅ ለሚነሳበት ትችት መልስ ለመስጠት ታስቦ የተሰራ ነው፡፡ ለዳር ድንበር የሚጨነቁትን ደግሞ ‹‹ወራሪዎች›› ብሎ ለመውቀስ፡፡ በነገራችን ላይ የሞሶሎኒ ፋሽስትና የሂትለር ናዚስት ፓርቲዎች በተመሳሳይ ዜማዎች ህዝብን አወናብደዋል፡፡ […]
