ሀገራዊና ክልላዊ ብሔርተኝነት ተጻራሪ የዕድገት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ነገስታት በጊዜ ሂደት ክልላዊ ብሔርተኝነትን እያሳነሱ ሀገራዊ ብሔርተኝነትን አዳብረዋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የተጠቀሙበት ዋና ዘዴ ከንጉሳዊ ቤተሰቦች ጀምሮ ብሔረሰቦች እርስ በርሳቸው ተጋብተው እንዲዋለዱ ማድረግ ነበር፡፡ ሌላው አቢይ ዘዴ የውስጥ አስተዳደራዊ አካባቢዎች በተቻለ መጠን በብሔረሰብ ስያሜ እንዳይጠሩ ማድረግ ነው፡፡ በተለይ የሁለቱ ታላላቅ ብሔረሰቦች አካባቢዎች ከዚህ ዓይነት ስያሜ የፀዱ እንዲሆኑ […]
