Quantcast
Channel: Freedom4Ethiopian
Viewing all articles
Browse latest Browse all 4543

አጋቾች በአስገድዶ መድፈር 4 ልጅ ያስወለዷት ኢትዮጵያዊት ወደ ሃገሯ ለመግባት በየመን እስር ቤት ትማቅቃለች

$
0
0
አጋቾች በአስገድዶ መድፈር 4 ልጅ ያስወለዷት ኢትዮጵያዊት ወደ ሃገሯ ለመግባት በየመን እስር ቤት ትማቅቃለች   በግሩም ተ/ሃይማኖት (ጋዜጠኛ) – ከየመን በጤና ችግር ምክንያት ሁሌም መሄድ ባልችልም በሄድኩ ቁጥር ሁሌም አሳዛኝ ነገር ነው እየገጠመኝ ያለው፡፡ የበዓል እለት እስረኞችን ለማየት እና በዓልን ለእነሱ ምሳ ማብላት አስበን ኢሚግሬሸን እስር ቤት ሄድን፡፡ ካጋጠሙኝ አሰቃቂ ነገሮች አንዱ አራት ልጅ ይዛ ብርድ ላይ እያደረች ያለች ሴት አወራኋት፡፡ አማርኛ መናገር የማትቸል በመሆኑ አስተርጓሚ ማግኘትም ችግር ሆኖብናል፡፡ የመን ውስጥ ያሉት ህገ- ወጥ አጓጓዦች ስደተኞችን እያፈኑ አሰቃይተው ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲያስልኩ ያስደርጋሉ፡፡እነዚህ አጋቾች ያገቷት አንዲት ኢትዮጵያዊት አንድ ልጅ ይዛ ነው ከሶማሊያ የተሻገረችው፡፡ ሶማሊያም አስገድዶ የመድፈር ሁኔታ ገጥሟት ወልዳ ነው የመን የገባችው፡፡ አሁን ደግሞ አግተው የያዟት ቦታ ሶስት ልጅ ወልዳለች፡፡ አራት በግዳጅ የመጡ ልጆች ይዛ ወደሀገር ልትገባ ነው፡፡ መጀመሪያ ልጆቹን እንዴት እንደያዘቻቸው ስላልገባኝ እና አራት መሆናቸውን አይቼ ስለሁኔታው ግርምት ጭሮብኝ ጠየኳት፡፡ ‹‹..ባህሩን ስሻገር የያዘኩት እንዷን ልጅ ነበር፡፡ ሀረድ የሚባለው ቦታ የሚያግቱት አፋኞች ያዙን የደረሰብኝን ተወው፡፡ ለሶስት አመት ተኩል እዛውአፍነው አቆዩኝ፡፡ በዚህን ጊዜ ነው እነዚህን ሶስት ልጆች የወለድኩት፡፡ እንዲያውም ሁለቱ ልጆች በ11 ወር ነው የሚበላለጡት፡፡ አራስ ቤት እያለሁምንም እረፍት የለኝም ነበር፡፡…››አንዷን ልጅ ሶማሊያ አግብተሽ ነው  የወለድሻት? የኔ ጥያቄ ነበር፡፡‹‹ እሷንም ሶማሊያ ውስጥ ተገድጄ በተደረገ ግንኙነት ነው የወለድኳት….›› ከዚህ በላይ መስማት አልቻልኩም፡፡ እንባምተናነቀኝ….እስኪ የምትለውን ቪዲዮውን እዩት…. posted by Aseged Tamene Filed under: Uncategorized Tagged: Abune Petros, Addis Ababa, Addis Ababa University, Advice, Africa, African Commission on Human and Peoples' Rights, Ethiopian government, Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front, human-rights, Politics of Ethiopia

Viewing all articles
Browse latest Browse all 4543

Trending Articles