ይሄውላችሁ ዛሬ ቤት ለቀኩ !! ምርጧን ቅዳሜ እቃ ከዛ ከዚህ በማንዘፋዘፍና ‹‹ቆምጨ›› ጋር በመነታረክ እንዳሳለፍኳት ስነግራችሁ በታላቅ ደስታ ነው ! ምክንያቱም ቅዳሜ ቀን ምንም ይፈጠር ምን ቅዳሜ መሆኑ በራሱ አንዳች የሰላም ስሜት አለውና …. ብለን ቅዳሜያችንን የነጀሱትን ነገራ ነገሮች ሁሉ አፉ ካልን በኋላ ስለነበረው ነገር ጨዋታችንን እንቀጥላለን ! (አሌክስ አብርሃም ነኝ ከአዲሱ ቤቴ ልበል እንዴ? […]
