ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመዋሃድ ንግግር እያደረገ ያለው የአረና ፓርቲ፣ ከሕወሃት ጋር ከፍተኛ የሰላማዊ ትግል ትንቅንቅ ላይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነዉ። በቅርቡ በአዲግራት ሊደረግ ታስቦ በነበረዉ ሕዝባዊ ስብስባ ከሌላ አኡራጃዎች የመጡ የሕወሃት ካድሬዎችና ዱርዬዉን ድንጋይ እየወረወሪ ሲበጠብጡ፣ የአመራር አባላትን ሲደበድቡ እንደነበረ የሚታወስ ነዉ። ህወሃት እነዚህ ዱርዮዎችን አሰማርቶ የሽብር ተግባራትን በመፈጸሙ ምክንያት፣ ስብሰባዉን ማድረግ ካለመቻሉ የተነሳ፣ […]
