ከዳዊት ሰለሞን በርብርብ የተረፈችው ወጣት ትናንት ከሰዓት አካባቢ አራት ኪሎ ለመንገደኞች መሸጋገሪያ ተብሎ በተሰራ ድልድይ ላይ የወጣች በሃያዎቹ መጨረሻ አካባቢ የምትገመት ሴት ራሷን ወደ መኪና መንገዱ ለመወርወር በምትዘጋጅበት ወቅት በአካባቢው የተገኙ ሰዎች ባደረጉት ርብርብ አደጋ ሳይደርስባት ለመትረፍ በቅታለች፡፡ ወጣቷን ለማትረፍ ሁለት የእሳት አደጋ መኪኖች ብዛት ያላቸው ፖሊሶች በስፍራው ተገኝተው የነበሩ ቢሆንም ወጣቷ ‹‹ሙስሊሞችን እወዳለሁ እነርሱን […]
