በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኤልኩራን በተሰኘ አካባቢ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ በማካሄድ ላይ የሚገኘው ‹‹ኒው ኤጅ›› የተሰኘው የእንግሊዝ ኩባንያ፣ በቆፈረው ‹‹ኤልኩራን ሦስት›› የተባለው ጉድጓድ ውስጥ የተፈጥሮ ዘይትና ጋዝ ፍሰት ታየ፡፡ ኩባንያው ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ጉድጓዱን በመቆፈር ላይ ይገኛል፡፡ የኩባንያው ዕቅድ 2,850 ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ መቆፈር ነው፡፡ ታማኝ ምንጮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኩባንያው 1,200 ሜትር ጥልቀት […]
