በስዑዲ ዐረቢያ በሥራ ተሠማርተው ከሚገኙት ቁጥራቸው በ 10 ሺዎች ከሚገመተው ኢትዮጵያውያን መካከል በተለያዩ ምክንያቶች ትክክለኛ መታወቂያ ሰነድ የሌላቸው ፤ እስከ ሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ ም፤ አሟልተው ካቀረቡ ፤ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ እንደሚያገኙ ፤ የስዑዲ ዐረቢያ መንግሥት ፣ ከ 3 ሳምንት ገደማ በፊት ልዩ «የምህረት አዋጅ» አውጥቷል። በዚህ አጋጣሚ ለመጠቀም ሠራተኞቹ ከአገራቸው ኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤት […]
