b ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ጊዜው ሴቶች ለውበታቸው አብዝተው የሚጨነቁበትና ለመዋብ የተለያዩ ጥረቶችን የሚያደርጉበት ነው፡፡ በጌጣጌጥ፣ በአልባሳት መዋቡ እንዳለ ሆኖ ለመለየት እስኪያስቸግር ድረስ የተለያየ ይዘትና የተለያየ ቀለም ያላቸው አርቲፊሻል ፀጉሮች፣ አርቲፊሻል ዳሌን የመሳሰሉ ነገሮችም ጊዜያቸውን ጠብቀው በስፋት መታየት ጀምረዋል፡፡ ፊትን ማውዛት ወይም ብሩህ ማድረግ በተለይም በዘይት ከጥንት ሥልጣኔ ጀምሮ ያለ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ወዝ ለመሰብሰብ፣ […]
