ሰዓታት ነጐዱ፡፡ ቀናትም ተቆጠሩ፡፡ የማሌዥያው ቦይንግ 777-200 አውሮፕላን 239 መንገደኞችን ይዞ ከኳላላምፑር ወደ ቤጂንግ ለማቅናት የአንድ ሰዓት በረራ አድርጐ ከተባለበት ቦታ ሳይደርስ ደብዛው ከጠፋ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ ፍለጋው ቢቀጥልም ዱካው አልተገኘም፡፡ አውሮፕላኑ ከራዳር እይታ መጥፋቱ በተነገረበት ዕለተ ቅዳሜ የመንገደኞች ቤተሰቦች የነበራቸው ተስፋ አሁን ደብዝዟል፡፡ ከጋዜጠኞች ጋር ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉ የነበሩ ቤተሰቦችም ‹‹የማሌዥያን አቪዬሽን ባለሥልጣን ጠይቁ፡፡ እኛ […]
