ከግብረሰዶማውያኑ ጀርባ ከጥቂት አመት በፊት በኢትዮጵያ በተለይ አዲስ አበባ የሚገኙ ግብረሰዶማውያን ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ በሸራተን ሆቴል የሃይማኖት አባቶች ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት በስፍራው ተገኝተዋል። ፕሮግራሙ ሊጀመር 15 ደቂቃ ሲቀረው በድንገት የደህንነት ሰዎች ይገቡና ጋዜጠኞች እንዲወጡ ያደርጋሉ። ቀጥሎ ለሃይማኖት መሪዎቹ « ይህን መግለጫ መስጠት አትችሉም» ተባሉ። « ማነው ከልካዩ?..» ሲሉ ጠየቁ፤ ጭራሽ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው። የተቃውሞ መግለጫው በዚህ መልኩ ተደናቀፈ። በመቀጠል ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተጠየቀ። የሸራተኑን መግለጫ ያደናቀፈው ባለስልጣን ጣልቃ […]
