‹‹ሞላ (አስገዶም) ግን ምን አይነት ሰው ነው? ንግግር አይችልም፡፡ ሚዲያ ላይ ሲቀረብ፣ ምን እንደሚነገርና ምን እንደማይነገር እንኳን ለይቶ አያውቅም፡፡ ‹‹መግለጫው››ን በአጋጣሚ አይቼ በመገረም ‹‹አጃኢብ›› ስል ነበር፡፡ [ፈገግታ ያጀበው ሳቅ] …ኢህአዴግም ሞላን ከሚያስከዳ ይልቅ ሌላ ሰው ቢሞክር ይሻለው ነበር፡፡ የሞላ ትርጉሙ አልታየኝም፡፡ የብርሃኑ (ነጋ/ፕሮፌሰር) ኤርትራ መምጣት ሞላን አነስተኛ (Insignificant) አድርጎታል፡፡ ሰውየው ለዓመታት እንዲሁ ተቀምጦ የነበረ ይመስለኛል፡፡ […]
