በአርባምንጭ ከተማ ብዙ ወጣቶች የግንቦት 7 አባል ናችሁ በሚል ሰበብ ተጠርጥረው ዕርቃናቸውን ግርፋትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸሙባቸው ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ። 20 አመት እድሜ ላይ የሚገኙ ዮሴፍ ይስሃቅና፣ እንዳሻው ወንድይፍራው ከዚህ በፊት በአርባምንጭ ከተማ ከጓደኞቻቸው ጋር ሲዝናኑ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ እያንዳንዳቸው በ2ሺ ብር ዋስትና እንደተለቀቁ፣ “ወያኔን ሰድበዋል፣ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ግንኙነት አላቸው” በሚል ሰበብ እንደተደበደቡ […]
