በሳውዲ የመን የሚገኙ የሳውዲ ከተሞችን በስራ ጉዳይ ተዘዋውሮ የማየት እድል አጋጥሞኛል ። በተዘዋወርኩባቸው አጋጣሚዎች ቁጥራቸው በርከት ያሉ በህገ ወጥ ድንበር ሰብረው የገቡና በህጋዊው መንገድ ወደ ሳውዲ ገብተው በዚያው የከተሙ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ኢትዮጵያውያን ወገኖቸን አግኝቼ ሳውዲ ስላደረሳቸው መንገድ ብዙ አውግተናል ። በተለይ በሕገ ወጡ የየመን ድንበር መጥተው በእረኝነትና በጉልበት ስራ ተሰማርተው የሚሰሩ ወንድሞቸን አግኝቼ በየመን […]
