የኢትዮጵያ መንግስት ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ እየወሰደ ያለው አፈናና እስራት አሳስቧት እንደሚገኝ አሜሪካ በድጋሚ ገለጠች። ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞም ከፕላኑ ያለፉ ብዙ ጉዳዮችን ያነገበ መሆኑንም የአሜሪካ ውጭ ጉዳት ሚኒስቴር ማክሰኞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል። በተያዘው ሳምንት ሰኞ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተካሄደውን ሰላማዊ […]
