ሁለቱም ሀገሪቱ የምትተማመንበት ድንግል መሬት፤ለም አፈር፤ከፍተኛ የቀንድ ከብት ክምችት ያለባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ራያዎችም አንደ ወልቃይቶች የተመሰከረላቸው ጀግኖች ናቸው፡፡ራያ በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ አካበባ በወሎ ክ/ሀገር ይገኛል፡፡ወልቃይት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ደቡብ ምዕራብ አካበባ በጎንደር ክ/ሀገር በወገራ አውራጃ ይገኛል፡፡ ራያም ወልቃይትም 1984 ዓ.ም በትግሬ ነፃ አውጭ ቡድን በወረራ ተይዘዋል፡፡ ሰሞኑን የወልቀይት ጀግኖች በማንነታቸው ላይ የተጫነውን ትግሬነት አራግፈው ዐማራ […]
