«ለአፍሪካዊያን ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው፣ የሚገባቸው ዲሞክራሲ ሳይሆን መልካም አስተዳደር ነው።» ኣለ አሉ… ፖለቲሺያን ኃይሌ ገብረሥላሴ። “ፖለቲሺያን” ስል እያፌዝኩት ወይም እያሽሟጠጥኩ አይደለም። ሁላችንም እንደምናውቀው ኃይሌ ኢትዮጵያንና እኛን ሕዝቦቿን በድል ካኮራበት ሙያው ወደ ፖለቲካው ተገብቷል። መብቱ ነው! ግና ገና ከጅምሩ በፖለቲካው መክሸፍ ሲያበዛ እየታዘብን ነው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙሪያ የሚሰጣቸው አስተያየቶች በእዝላልነት ይሁን ወይም ፖለቲካውን ባለመረዳት አላውቅም ብዙውን […]
