ድርቁ ለመከላከል ተብሎ እየመጣ ያለው የእርዳታ እህልና እርዳታ ጠባቂ ህዝብ ቁጥር ስለማይመጣጠን፣ የመጣው እርዳታ ከከፍተኛ ባለ ስልጣናት እስከ የቀበሌ ካድሬዎች እየዘረፉትና ኢ_ፍትሓዊ በሆነ መንገድ ስለሚከፋፈል እርዳታው የህዝቡና እንስሳቱ ሂወት ከሞት ሊታደግለት ኣልቻለም። በሰው ሂወት እየደረሰ ያለው ኣደጋ በህፃናትና ኣረጋውያን የሚብስ ሲሆን ከእንስሶች ደግሞ በፍየሎችና በጎች የበለጠ ኣደጋ ኣስከትለዋል። በረሃብ እየሞተ ያለው የሰው ስምና ፎቶ በፌስቡ […]
