ሰሞኑን በምሽራቅና ምዕራብ ሃረርጌ በሚገኙ የገጠር መንደሮች ዳግም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በሳምንቱ መገባደጃ ወደ በርካታ አካባቢዎች በመዛመት ላይ መሆኑ ተገልጿል። በስፍራው በመካሄድ ላይ ያለን ግድያና እስራት ለማውገዝ አደባባይ በወጡ ነዋሪዎች ላይ እሁድና ሰኞ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ቁጥሩ በአግባቡ ሊታወቅ ያልቻለ ሰው መገደሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ይኸው ተቃውሞ ሰኞ በአዲስ መልክ በምስራቅ ወለጋ አካባቢም […]
