ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደ አገር ውስጥ የገቡ ሞባይልን ጨምሮ ተንቀሳቃሽ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎችን ከአገልግሎት ለማስወጣት የሚያስችለውን የመገልገያ ቁሶች ምዝገባ፣ ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣዩ ሳምንት በሙከራ ደረጃ በሰራተኞቹ መገልገያዎች ላይ ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል ፡፡ ቴሌ ኮም የመገልገያ ቁሶቹን ምዝገባ የሚያከናውነውም ደንበኞቹ ወደ ድርጅቱ ሳይሄዱ ባሉበት ቦታ ሆነው ነው ተብሏል፡፡ድርጅቱ ይህንን ለማድረግ የሚያስችለውን የመመዝገቢያ ቴክኖሎጂ ከቱርክ የሶፍት ዌር […]
