ያዥልኝ ቀጠሮ፣ አይሽ አይሽና፣ መልካም ልደትና ሌሎችም ተወዳጅ ሙዚቃዎችን በጊታር በመጫወት የሚታወቀው ድምፃዊ መስፍን አበበ ትናንት በድንገተኛ ህመም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ዛሬ ከንጋቱ 11 ሰዓት ገደማ ህይወቱ ማለፉን ለመረዳት ተችሏል። መስፍን አበበ ከደሴ ወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ባንድ ጋር በመሆን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በመዘዋወር ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር፡፡ ቦክስ ጊታሩን በመያዝ 22 ያህል […]
