የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያደረጉትን የካቢኔ አባላት ሹም ሽርን ተችተዋል፡፡ መሰረታዊ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች ሹም ሽር ሀገሪቱ አሁን ያለችበትን የፖለቲካ ቀውስ አይፈታም ሲሉ አዲሱን የሚኒስትሮች ሹመት አልተቀበሉትም፡፡ ህዝብ እየጠየቀ ያለው የፖሊሲ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች መለዋወጥ ለውጥ አያመጣም ብለዋል፡፡ ከጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ጋር ቃለምልልሰ ያደረጉት ዶ/ር መረራ ጉዲና “ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም ” […]
