ዳግማዊ ተሰማ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሃላፊና የምክር ቤት አባል የነበረው ዳግማዊ ተሰማን እኔ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አናንያ ሶሪ፣ ሃብታሙ ምናለና ፍቃዱ በቀለ ካዛንቺስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጠይቀነው ነበር። ዳግምም “ከታሰርኩ ዛሬ ሳምንቴ ነው። እስከዛሬ ማንም ያነጋገረኝ አካል የለም። ስም፣ አድራሻዬንና የትምህርት ደረጃዬን ብቻ ነው የተጠየኩት። ኮማንድ ፖስቱ ገና አልተደራጀም […]
