በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ የእንቃሽ ቀበሌ የዐማራ ገበሬዎችን ትጥቅ ለመንጠቅ የተንቀሳቀሰው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ በምርኮና በሞት ተደምስሷል፡፡ ከቦታው በስልክ ያነጋገርናቸው የጎበዝ አለቆች ‹‹ሆን ብለው አዝመራችን በምንሸክፍበት በዚህ ወቅት መሣሪያ ለመግፈፍ መጡብን፤ እኛም ገጥመን ፈጀናቸው›› ብለዋል፡፡ ከትናንት ጥቅምት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ከሰዐት በኋላ ጀምሮ ሌሊቱን ባደረው ጦርነት 50 የሚሆኑ ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ተማርከዋል፡፡ […]
