በአሁኑ ሰዓት የህወሓት አገዛዝ የገባበት ቀውስ እየተወሳሰበ ነው። አሁን እውነተኛ የመንግሥት ስልጣን ያለው በሳሞራ የኑስ እጅ ውስጥ ቢሆንም እንኳን ተቀናቃኙ ጌታቸው አሰፋ ሽንፈቱን ሙሉ በሙሉ አልተቀበለም። የሳሞራ የኑስ ቀኝ እጅ የሆነው በገብሬ አድሀና (ዲላ) የሚመራው ወታደራዊ መረጃ የጌታቸው አሰፋን “የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን” ሊውጥ አፉን ከፍቷል። ጌታቸው የኃይለማርያምን ካቢኔ ከቀውስ የመውጫ ቀዳዳ ሊያደርገው እየጣረ ነው። […]
