የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ከህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ የተፈጸመው ግድያ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ሃሙስ ያቀረበው ጥያቄ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ሂውማን ራይትስ ዎች አሳሰበ። ፓርላማው ያቀረበው ይኸው ወቅታዊ ጥሪ ጉዳዩ የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በቀጣዩ ወር በጀኔቭ ከተማ በሚካሄደው ጉባዔ ላይ ተጨማሪ እርምጃ እንዲወስድ ሊያደርግ የሚያስችል መሆኑን በድርጅቱ የአፍሪካ ቀንድ ተመራማሪ የሆኑት ፊሊክስ ሆንር አስታውቀዋል። […]
