በግብርና ለሚተዳደረው ህዝባችን የእርሻ፣ የቡቃያ፣ የተስፋ ወቅት ነበር። የጎንደር አርሶ አደር ግን ለዛ አልታደለም። በድንበሩ፣ በባድማው፣ በርስቱ፣ በራስ መጠበቂያው በብረቱ በጠመንጃው፣ በቤተሰቡ፣ በህይወቱ መጡበት። ተው አለ በሰላም ጠየቀ መልሳቸው ግድያ ሆነ። እረዥሙ ትእግስት ተሟጠጠ። እጅ ጠምዝዘን እንውሰድህ ያሉት ኮሎኔል ደመቀ የማን ልጅ እንደሆንኩ ላስታውሳቹህ ብሎ ችቦውን ለኮሰው። ወያኔ ፍርድ በማጓተት ጨለማ ቤት አስሮ አሁንም ለሐምሌ […]
