ደ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳሉት ‹‹የጠላቶቻችንን ቃሎች ከምናስታውስ ይልቅስ የወዳጆቻችንን ዝምታ እናስበዋለን›› እኔ ደግሞ፤ የጠላቶቻችንን ተግባርና ግፋዊ ድርጊት እያሰብነው ይቅርታንም እንቸራለን የሚያደርጉትን አያውቁትምና፡፡ የሚፈጸመውን ግፍ፤የሕዝብ መብት ገፈፋ፤ የሰብአዊ መብት መጣስን፤የፍትህን እጠትና ሌላውንም ሁሉ እያዩ እነዳላዩ እየሰሙ እንዳልሰሙ በመሆን ጀሯቸውን የጠቀጠቁትን፤ አፋቸውን የለጎሙትን፤ አንደበታቸውን የዘጉትን ወዳጀቻችንን ግን ይቅርታም አልቸር ልረሳውም አልፈቅድም፡፡ በእስር ስር ያሉትን ዘወትር አብረናቸው […]
